ኢዮብ 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣ ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው አድገውና ተደላድለው ሲኖሩ ለምን ያያሉ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘራቸው በፊታቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፤ ልጆቻቸውም በዐይናቸው ፊት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው። |
አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።