La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 21:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የክፉዎች መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቁጣው መከራ የከፈላቸው፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው? የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣ መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ለመሆኑ የክፉ ሰዎች መብራት ጠፍቶ ያውቃልን? መቅሠፍትስ በእነርሱ ላይ ወርዶ ያውቃልን? እግዚአብሔር በቊጣው ቀጥቶአቸው ያውቃልን?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኃ​ጥ​ኣን መብ​ራት ትጠ​ፋ​ለች፤ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ትመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለች። የበ​ቀል ቍጣም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኃጥአን መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው፥

Ver Capítulo



ኢዮብ 21:17
13 Referencias Cruzadas  

ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥ ከዓለምም ያሳድዱታል።


ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚተርፍ፥ በቁጣው ቀን እንደሚድን።


የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ከላይ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ርስትስ ከአርያም ምንድነው?


መዓትስ ለኃጢአተኛ፥ መገለልስ ለሚበድሉ ሰዎች አይደለችምን?


በኃጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት፥ በጌታ የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከብበዋል።


ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።


ለክፉ ሰው የወደፊት ተስፋ የለውምና፥ የክፉዎች መብራት ይጠፋልና።


ሞኞቹ ብልሆቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነውና ከዘይታችሁ ስጡን’ አሉአቸው።


የዚያ ባርያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፤ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርጋል።