‘የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወስድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም፤
ኢዮብ 20:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱም ንብረት ይሰናበታል፥ በቁጣው ቀን በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ቤቱን ጐርፍ፣ መኖሪያውንም ወራጅ ውሃ ይወስድበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔርም የቊጣ ቀን የቤቱ ንብረት ሁሉ በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥፋትም ቤቱን ወደ ፍጻሜ ያመጣታል። የቍጣ ቀንም ትመጣበታለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤቱም ባለጠግነት ይሄዳል፥ በቍጣው ቀን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያልፋል። |
‘የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወስድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም፤
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።
በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ አንዳች ግን አትቀምሰውም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ ለአንተም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህ ማንም አይኖርም።
ይህን የሚያህል ታላቅ ሀብት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤