ኢዮብ 20:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆዱን ሳያጠግብ እግዚአብሔር የቁጣውን ትኩሳት ይሰድድበታል፥ በምግብ መልክም ያዘንብበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆዱን በሞላ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚነድድ ቍጣውን ይሰድበታል፤ መዓቱንም ያወርድበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በልቼ እጠግባለሁ ሲል እግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣውን ያወርድበታል። መዓቱንም በእርሱ ላይ ያዘንብበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሆዱን ቢያጠግብ፥ የመዓት መቅሠፍት ይጨመርበታል፤ የሕማሙም ሥቃይ ይጸናበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሆዱን ሳያጠግብ እግዚአብሔር የቍጣውን ትኵሳት ይሰድድበታል፥ ሲበላም ያዘንብበታል። |
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።
“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”
ሕዝቡንም እንዲህ በላቸው፦ ለነገ ተቀደሱ፥ ሥጋንም ትበላላችሁ ምክንያቱም እንዲህ እያላችሁ ያለቀሳችሁት ለቅሶ ወደ ጌታ ጆሮ ደርሶአልና፦ ‘የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብጽ ሳለን በዚያ ደኅና ነበርን፤’ ስለዚህ ጌታ ሥጋን ይሰጣችኋል፥ ትበላላችሁም።