ኢዮብ 20:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንድመልስ ሐሳቤ ይገፋፋኝል፥ ስለዚህም ውስጤ መታገሥ አቅቶታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እጅግ ታውኬአለሁና፣ ሐሳቤ መልስ እንድሰጥ ይጐተጕተኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! የሕሊናዬ ብስጭት መልስ እንድሰጥህ አስገደደኝ፤ ስለዚህም ነው ለመናገር የቸኰልኩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደዚህ እንደምትመልስ አልጠረጠርሁህም ነበር፤ በዕውቀትም ከእኔ አትሻልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በውስጤ ስላለው ችኰላ አሳቤ ትመልስልኛለች። |
እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።