ኢዮብ 20:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹ ድሆቹን ይክሳሉ፥ በገዛ እጆቹ ሀብቱን ይመልሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቹ ለድኾች ካሳ መክፈል አለባቸው፤ እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቹ እየተለማመጡ አባታቸው ከድኾች በግፍ የቀማውን ገንዘብ ይከፍላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተዋረዱ ሰዎች ልጆቹን ያጠፋሉ፤ እጆቹም የኀዘን እሳትን ያቀጣጥላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹ ድሆቹን ያቈላምጣሉ፥ እጁ ሀብቱን ይመልሳል። |
ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ! ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ፤” አለው።