ክብሬን ገፈፈኝ፥ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
ክብሬን ገፍፎኛል፤ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዷል።
ክብሬን ከራሴ ላይ ገፎ አዋረደኝ።
ክብሬን ገፈፈኝ፤ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
አማካሪዎችንም እራቁታቸውን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ሞኝ ያደርጋል።
ካህናትን እንደ ምርኮኛ ይወስዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።
በቆዳዬ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ አኖርሁ።
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።
አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ በቀባኸውም ላይ በቁጣ ተነሣህ።
የአገልጋይህን ኪዳን አፈረስህ፥ ዘውዱንም በምድር አረከስህ።
የሰይፉንም ረድኤት መለስህ፥ በጦርነትም ውስጥ አልደገፍኸውም።
ሃብት ለዘለዓለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና።
እናንተ ግን የጌታ ካህናት ትባላላችሁ፤ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፥ በሀብታቸውም ትከብራላችሁ።
አክሊል ከራሳችን ወድቆአል፥ ኃጢአት ሠርተናልና ወዮልን!
የኤፍሬምም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፤ መውለድና መፅነስ ማርገዝም አይሆንላቸውም።