ኢዮብ 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውነቱ ክፍሎች ይጠፋሉ፥ የሞትም የበኩር ልጅ ሰውነቱን ይበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደዌ ቈዳውን ይበላል፤ የሞት በኵርም ቅልጥሙን ይውጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሽታ ሰውነቱን ያመነምነዋል፤ ሞትም ጨርሶ ይረከበዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጭኖቹ ይበሰብሳሉ። ሞትም መልካም ሕዋሶቹን ይበላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውነቱ ብልቶች ይጠፋሉ፥ የሞትም በኵር ልጅ ብልቶቹን ይበላል። |
ጌታም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዐይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
አየሁም፤ እነሆም የገረጣ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።