ኢዮብ 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥ በፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላክ ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሰዎች መዘባበቻ አደረገኝ፤ ሰዎቹም በፊቱ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሕዛብም ምሳሌ አደረግኸኝ፤ መሳቂያና መዘባበቻም ሆንኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥ በፊቱ ላይ ጺቅ እንደሚሉበት ሰው ሆንሁ። |
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።”