ኢዮብ 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ከንቱ ቃል መጨረሻ የለውምን? ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሣሣህ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን? ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ከንቱ ንግግራችሁ መጨረሻ የለውምን? ከእኔ ጋር ይህን ያኽል ለመከራከር ያነሣሣችሁ ምክንያት ምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጣላችሁን ሁሉ ያለ ልክ ትናገራላችሁ፦ ትከራከሩኝ ዘንድስ ምን አስቸገርኋችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ከንቱ ቃል ይፈጸማልን? ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሣሣህ ምንድር ነው? |