ነገር ግን በእጄ ዓመጽ የለም፥ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።”
ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
ይህ ሁሉ ሲሆን የፈጸምኩት በደል የለም፤ ጸሎቴንም ወደ እግዚአብሔር የማቀርበው በንጹሕ ልብ ነው።
ሆዴ በልቅሶ ተቃጠለ፤ የሞት ጥላን በቅንድቦች ላይ አያለሁ፤
ነገር ግን በእጄ ዓመፅ የለም፥ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
ክፉ ሰው ዕድሜ ልኩን ሲሠቃይ ይኖራል፥ እንዲሁም ግፈኛ በተመደቡለት ዓመታት በሙሉ።
የአምላክ አልባ ሰው ጉባኤ ፍሬ የለውም፥ የጉቦ ድንኳኖችንም እሳት ትበላለች።
“ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይኑር።
ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥ አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም።
‘እኔ ንጹሕ ነኝ፥ በደል የለብኝም፤ ያለ እንከን ነኝ፥ ኃጢአትም የለብኝም፥
የዳዊት ጸሎት። አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ተንኰል ከሌለበት ከንፈር የሚወጣውንም ጸሎቴን አድምጥ።
የኀጥኣን መሥዋዕት በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።
ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ ራሳቸውንም በሠሩት መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።
ሰውም ሆነ እንስሳ በማቅ ይሸፈኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎች ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በመዳፋቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።
እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው።