ኢዮብ 16:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዐይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቷል፤ ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፏል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊቴ በልቅሶ ቀላ ድቅድቅ ጨለማም ቅንድቦቼን ሸፈናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍርበቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከራዬ በመሬት ላይ በዛች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዓይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥ |
ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤
ዔ። የሚያጽናናኝ ነፍሴንም የሚያበረታት ከእኔ ርቆአልና ስለዚህ አለቅሳለሁ፥ ዓይኔ፥ ዓይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆቼ ጠፍተዋል።