እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።
ኢዮብ 14:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ ጐርፍም ዐፈርን ዐጥቦ እንደሚወስድ፣ አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃ ድንጋይን እየቦረቦረ እንደሚጨርስ፥ ኀይለኛ ዝናብም መሬትን እንደሚሸረሽር፥ አንተም እንዲሁ የደካማን ሰው ተስፋ ታጠፋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ውኆች ድንጋዮችን ይፍቃሉ፤ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፤ እንዲሁ አንተ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ። |
እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።