ኢዮብ 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው በፊቱ አይቀርብምና፥ እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአተኛ በርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፣ ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛ ሰው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ስለማይችል ምናልባት ይህ ድፍረቴ የመዳን ምክንያት ሊሆን ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኀኒት ይሆንልኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል። |
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”