ኢዮብ 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ያስወግዳል፥ መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዓለም መሪዎችን ማስተዋል ይነሣል፣ መንገድ በሌለበት በረሓም ያቅበዘብዛቸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎች ማስተዋል እንዲጐድላቸውና መንገድ በሌለበት በበረሓ እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድር አለቆች ማስተዋልን ይለውጣል። በማያውቁት መንገድም ያቅበዘብዛቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል። |
ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።