Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 12:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሕዛብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ እነርሱንም ያጠፋል፥ አሕዛብንም ያሰፋል፥ እነርሱንም ያፈልሳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሕዝቦችን ታላቅ ያደርጋል፤ መልሶም ያጠፋቸዋል፤ ሕዝቦችን ያበዛል፤ ያፈልሳቸዋልም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 መንግሥታትንም ታላላቅ ያደርጋቸዋል፤ ያጠፋቸዋልም፤ ሕዝብን ያበዛል፤ ይበታትናልም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አሕ​ዛ​ብን ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ልም፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አሕዛብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ እነርሱንም ያጠፋል፥ አሕዛብንም ያሰፋል፥ እነርሱንም ያፈልሳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 12:23
13 Referencias Cruzadas  

ሕዝብን አበዛህ፥ አቤቱ ጌታ፥ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፥ የአገሪቱንም ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።


ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፤ የከበዳቸውን ቀንበር፤ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፤ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።


ታናሹ ለሺህ፥ የሁሉም ታናሹ ኃያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ ጌታ በዘመኑ ይህን በፍጥነት አደርገዋለሁ።


ባረካቸውም እጅግም በዙ፥ እንስሶቻቸውንም አላሳነሰባቸውም።


በፉጨት እጠራቸዋለሁ፤ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስለምቤዣቸው እንደ ቀድሞው ብዙ እጥፍ ይሆናሉ።


የሰማይን ሠራዊት መቁጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባርያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።”


ከእርሱም ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች የሐሤት ድምፅ ይወጣል፤ እኔም አበዛቸዋለሁ አያንሱምም፥ እኔም አስከብራቸዋለሁ ታናሽም አይሆኑም።


ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፥ ባረክሁትም አበዛሁትም።


በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያቈጠቁጣል፥ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።


እግዚአብሔርም ለአዋላጆቹ መልካም ነገርን አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፥ እጅግም ብርቱ ሆነ።


ነገር ግን የእስራኤል ትውልዶች ፍሬያማ ነበሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ እጅግም በረቱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።


ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።


እነርሱ በጭቈና፥ በስቃይና በኃዘን ተዋርደው እያነሱ ሄዱ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios