ኢዮብ 11:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሆኖም፥ ልብህን የቀና ብታደርግ እጅህንም ዘርግተህ ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ |
በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን መንጋ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፥ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።
ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ከከተማ እንደ ወጣሁ እጄን ወደ ጌታ እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ የጌታ እንደ ሆነች እንድታውቅ፥ ነጎድጓዱ ይቆማል፥ በረዶውም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በፍጹም ልባችሁ ወደ ጌታ የምትመለሱ ከሆነ፥ ባዕዳን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለጌታ አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።