ኢዮብ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ሲወለድ፥ ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጅል ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ፣ የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በከንቱ ነገርን የሚፈልግ ሰው፥ ከሴትም የሚወለድ ሟች የሜዳ አህያን ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜዳ አህያ ግልገል ሰው ሆኖ ቢወለድ፥ ያን ጊዜ ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል። |
በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፤ ከጋለው ምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል።
በእነዚህም ልጆች መካከል እኛም ሁላችን፥ የሥጋችንንና የህዋሳቶቻችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበር፤ ደግሞም እንደ ሌሎቹ በባሕርያችን የቁጣ ልጆች ነበርን።