ኢዮብ 11:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይረቡ ሰዎችን ያውቃልና፥ በደልንም ሲያይ ዝም ብሎ አይመለከትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የማይጠቅሙ ሰዎችን ያውቃቸዋል፤ በደልን በሚያይበት ጊዜ ዝም ብሎ አይመለከትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ የኃጥኣን ሰዎች ሥራን ያውቃል፤ በደልንም ቢያይ ዝም ብሎ አይመለከትም፤ ይህንም አስተዋይ ሰው ያስተውላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናምንቴዎችን ሰዎች ያውቃልና፥ በደልንም ሲያይ ዝም ብሎ አይመለከትም። |
አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥ ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
ዐይኖችህ ክፉ እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፥ ክፉ ሥራም መመልከት አትችልም፤ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉዎቹ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆኑትን ሲውጡ ለምን ዝም ትላለህ?
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።