ኢዮብ 11:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣ የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር መጥቶ ቢያስር፥ ወደ ፍርድ ሸንጎም ቢያቀርብ፥ ማን ይከለክለዋል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ሁሉን ቢገለብጥ፥ ምን አደረግህ? የሚለው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው? |
“በፊላደልፊያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ‘ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፥ የዳዊትም መክፈቻ ያለው፥ ሲከፍትም፥ ማንም የማይዘጋው፤ ሲዘጋም ማንም የማይከፍተው፤ እርሱ እንዲህ ይላል’፦