የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
ጥቂት የሆነው ዘመኔ እያለቀ አይደለምን? ከሥቃዬ ፋታ እንዳገኝ ተወት አድርገኝ፤
የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? በዚህች አጭር ዘመን ጥቂት እንድደሰት እባክህ ተወኝ!
የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ፤
የሕይወቴ ዘመን ጥቂት አይደለምን?
እንዳልነበረ በሆንሁ፥ ከማኅፀንም ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
እጅህን ከእኔ አርቅ፥ ግርማህም አታስደንግጠኝ።
“ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ በመከራም የተሞላ ነው።
እኛ የትናንት ብቻ ነን፥ ምንም አናውቅም፤ ቀኖቻችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ናቸውና።
እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፥ ነገር ግን መራራን ነገር አጥግቦኛል።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ፥ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ረጋፊ እንደሆንኩ አውቅ ዘንድ።