ኢዮብ 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ ግን በልብህ ሸሸግህ፤ ነገሩ በሐሳብህ እንደ ነበር ዐውቃለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለካስ እነዚህን ነገሮች በልብህ ሰውረኻቸው ኖሮአል፤ ዓላማህም ይህ እንደ ሆነ ዐወቅሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሁሉ በአንተ ዘንድ አለ። ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል፥ የሚሳንህም እንደ ሌለ አውቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ። |
“እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።