Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 45:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አዳኙ የእስራኤል አምላክ ሆይ፤ አንተ በእውነት ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አዳኙ የእስራኤል አምላክ ሆይ! በእውነት የአንተ ሥራ ከሰው ማስተዋል የተሰወረ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መድ​ኀ​ኒት አም​ላክ እንደ ሆንህ አላ​ወ​ቅ​ን​ህም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 45:15
24 Referencias Cruzadas  

ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን ጌታን እጠብቃለሁ፤ እርሱንም ተስፋ አደርጋለሁ።


አቤቱ፥ ንቃ፥ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።


ኃጢአት ስለ ሞላበት ስግብግብነቱ ተቈጣሁት፤ ቀጣሁት፤ ፊቴንም በቁጣ ከእርሱ ሰወርኩ፤ እርሱ ግን በመንገዱ ገፋበት።


ጽድቄን አቀርባለሁ፥ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቼአለሁ።


የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነበረ፥ መብረቆች ለዓለም አበሩ፥ ምድር ተናወጠች ተንቀጠቀጠችም።


እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና።


ጌታ ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፥ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አትዋረዱም።


እኔ፥ እኔ ጌታ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።


እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ ጌታ መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ እሰጣለሁ።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


አለቆች ቀደሙ፥ መዘምራንም ተከተሉ፥ ከበሮን በሚመቱ በቈነጃጅት መካከል።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።


ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት እንዲሰጥ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።


ሴቲቱንም “አሁን የምናምነው በቃልሽ ምክንያት አይደለም፤ እኛ እራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱ በእውነት የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን፤” ይሉአት ነበር።


የአሕዛብንም ወተት ትጠጫልሽ፥ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም ጌታ፥ የያዕቆብ ኃያል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደሆንሁ ታውቂያለሽ።


ኢየሱስም መልሶ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


ይህም ለሠራዊት ጌታ በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው ምክንያት ወደ ጌታ በመጮኻቸው፥ እርሱ መድኃኒትንና ኃያልን ሰዶ ያድናቸዋል።


እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ።


እርሱን እንዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!


ወደሚሠራበት ወደ ግራ ብሄድ አይታየኝም፥ በቀኜም ይሰወራል፥ አላየውምም፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios