ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።
ኢዮብ 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና እየጠጡ ሳሉ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸኛው መልእክተኛም ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ “ልጆችህ በሙሉ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ይደሰቱ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ገና ይህን ሲናገር አራተኛው መልእክተኛ መጥቶ ለኢዮብ እንዲህ አለው፥ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ሲበሉና የወይን ጠጅ ሲጠጡ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፥ |
ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።
እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው።
እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”
ወንዶች ልጆቹም ሄደው በየተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያሰናዱ ነበር፥ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ልከው ይጠሩአቸው ነበር።
የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ መልካሙ ሰው እንደ ኃጢአተኛው፥ የሚምለው ሰው መሐላን እንደሚፈራው ነው።
ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንደኛው ሯጭ ሌላውን ሯጭ አንዱም መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ለመገናኘት ይሮጣል።
ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።