Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር አራ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ በታ​ላቅ ወን​ድ​ማ​ቸው ቤት ሲበ​ሉና የወ​ይን ጠጅ ሲጠጡ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና እየጠጡ ሳሉ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ይኸኛው መልእክተኛም ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ “ልጆችህ በሙሉ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ይደሰቱ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 1:18
17 Referencias Cruzadas  

ወን​ዶች ልጆ​ቹም ሄደው በየ​ተራ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ቤት ግብዣ ያደ​ርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ይበ​ሉና ይጠጡ ነበር።


አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የኢ​ዮብ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች በታ​ላቅ ወን​ድ​ማ​ቸው ቤት ይበ​ሉና የወ​ይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።


ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።


ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይነ​ግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመ​ገ​ና​ኘት፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን ለመ​ገ​ና​ኘት ይሮ​ጣል፤ ከተ​ማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይ​ዛ​ለ​ችና፤


ባለ​ፈም ጊዜ ይወ​ስ​ዳ​ች​ኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያል​ፋል፤ በሌ​ሊት ክፉ ተስፋ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ያዘ​ና​ችሁ፥ መስ​ማ​ትን ተማሩ።”


በሁ​ሉም ከን​ቱ​ነት አለ፥ የጻ​ድ​ቁና የበ​ደ​ለ​ኛው፥ የመ​ል​ካ​ሙና የክ​ፉው፥ የን​ጹ​ሑና የር​ኩሱ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ሠ​ዋ​ውና የማ​ይ​ሠ​ዋው፥ የመ​ል​ካ​ሙና እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው፥ የመ​ሐ​ላ​ኛ​ውና እን​ዲሁ መሐ​ላን የሚ​ፈ​ራው ድርሻ አንድ ነው።


በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም።


ልጆቹ ቢበዙ ለጥ​ፋት ይሆ​ናሉ፤ ቢያ​ድ​ጉም ለማ​ኞች ይሆ​ናሉ።


“ዛሬም ዘለ​ፋዬ ከእጄ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ። እጁ​ንም በእኔ ላይ አከ​በደ፥ አስ​ለ​ቀ​ሰ​ኝም።


በጦር ከበ​ቡኝ፤ ኵላ​ሊ​ቴ​ንም ወጉኝ፤ እነ​ር​ሱም አል​ራ​ሩ​ል​ኝም፤ ሐሞ​ቴ​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ።


ልጆ​ችህ በፊቱ በድ​ለው እንደ ሆነ፥ እርሱ በበ​ደ​ላ​ቸው እጅ ጥሎ​አ​ቸ​ዋል።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሦስ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ፈረ​ሰ​ኞች በሦ​ስት ረድፍ ከብ​በው ግመ​ሎ​ችን ማር​ከው ወሰዱ፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios