ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።
ኢዮብ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ንብረቱም በምድር ላይ በዝቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱና በቤተ ሰቦቹ፣ ባለው ንብረትስ ሁሉ ዙሪያ ዐጥር ሠርተህለት የለምን? የበጎቹና የላሞቹ መንጋ ምድርን ሁሉ እስኪሞሉ ድረስ የእጁን ሥራ ባርከህለታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አንተን የሚፈራህ እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ንብረት ሁሉ በደኅና ስለ ጠበቅህለት፥ የሚሠራውንም ሁሉ ስለ ባረክህለትና ብዙ የከብት መንጋ ስለ ሰጠኸው አይደለምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱም በምድር ላይ በዝቶአል። |
ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።
ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?”
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ የግብፃዊውን ቤት ባረከ፥ የጌታም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት።
ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
ጌታም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፥ ዐሥራ አራት ሺህም በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት።
መሬቱን ቈፈረ፤ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤ የወይን መጭመቂያ ጉድጓድም አበጀ፤ ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ አሰበ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።
ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ እንዲሁም የምድርህንም ፍሬ፥ እህልና ወይንህን፥ ዘይትህንም፥ በከብትም ብዛት በበግም መንጋ አብዝቶ ይባርክልሃል።