ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ፤ ኰርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር።
ኤርምያስ 52:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ሰሎሞንም ለጌታ ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኩሬ፥ ከኩሬውና ከውኃ ማመላለሻ ፉርጎዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ ከናስ ለተሠረሩ ዕቃዎች ሁሉ መመዘኛ ሚዛን አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከናስ ያሠራቸው፦ ሁለቱ ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፣ ከሥሩ ያሉት ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችና ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሁለቱን ምሰሶዎች፥ አንዱን ገንዳ፥ ዐሥራ ሁለት በኰርማ ቅርጽ ከነሐስ የተሠሩትን የገንዳ ማስቀመጫዎች፥ ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ አሠርቶአቸው የነበሩትን ተሽከርካሪ መቆሚያዎችን ሁሉ ወሰደ። እነዚህ ዕቃዎች የተሠሩበት ነሐስ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሊመዘን አልተቻለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ አንዱንም ኵሬ፥ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ የናስ ዕቃዎች ሁሉ ሚዛን አልነበራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፥ አንዱንም ኵሬ፥ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን አሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፥ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረም። |
ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬዎች ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ፤ ኰርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር።
ከነሐስ የተሠራው ይህ ሁሉ ዕቃ እጅግ ብዙ ስለ ነበር፥ ሰሎሞን በሚዛን እንዲለካ አላደረገውም፤ ስለዚህ ክብደቱ ምን ያኽል እንደሆነ ተወስኖ አልታወቀም።
ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ታላቁን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፥ በክብደታቸው ምክንያት ሊመዝኑአቸው አልቻሉም።
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለጌታ ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ በሚዛንም የማይመዘን ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም በዚያ ላይ ጨምርበት።
ከለዳውያንም በጌታ ቤት የነበሩትን የናስ ዓምዶች በጌታም ቤት የነበሩትን የውኃ ማመላለሻ ፉርጎዎችንና የናሱን ኩሬ ሰባበሩ፥ ናሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱ።