እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ፥ አበባው ያበበ የወይንም ፍሬ ሲይዝ፥ የወይኑን ዘንግ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ ጫፎቹንም መልምሎ ያስወግዳል።
ኤርምያስ 51:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ፣ የእህል መውቂያ ዐውድማ ናት፤ የመከር ወራቷም ፈጥኖ ይደርስባታል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የባቢሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረገጠ አውድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አውድማ እንደ ተረገጠ ጊዜ፥ እንዲሁ የባቢሎን ልጅ ናት፥ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል። |
እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ፥ አበባው ያበበ የወይንም ፍሬ ሲይዝ፥ የወይኑን ዘንግ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ ጫፎቹንም መልምሎ ያስወግዳል።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ገለዓድን የብረት ጥርስ ባለው መውቅያ አበራይተውታልና ስለ ሦስት የደማስቆ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
የጽዮን ልጅ ሆይ ተነሺ አሂጂ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ኮቴሽንም ናስ አደርጋለሁና፤ ብዙ ሕዝቦችን ታደቅቂአለሽ፤ እኔም ትርፋቸውን ለጌታ፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አውለዋለሁ።
እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ ተዉአቸው፤ በመከር ጊዜ አጫጆቹን “አስቀድማችሁ እንክርዳዱን በእሳትም ለማቃጠል ሰብስባችሁ በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱት፤ እላቸዋለሁ።”