La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 51:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቀስተኛው ቀስቱን አይገትር ጥሩሩንም ለብሶ አይነሣ፤ ለጐልማሶችዋ አትዘኑ ሠራዊትዋንም ሁሉ አጥፉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቀስተኛው ቀስቱን እስኪገትር፣ የጦር ልብሱንም እስኪለብስ ፋታ አትስጡት፤ ለወጣቶቿ አትዘኑ፤ ሰራዊቷንም ፈጽማችሁ አጥፉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወታደሮችዋ ቀስታቸውን እስኪገትሩና ወይም የጦር ልብሳቸውን እስኪለብሱ ጊዜ አትስጡአቸው፤ ለወጣቶችዋ በመራራት ምሕረት አታድርጉ፤ ሠራዊትዋን በሙሉ ደምስሱ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በቀ​ስት ወር​ዋ​ሪው ላይ፥ በጥ​ሩ​ርም በሚ​ነ​ሣው ላይ ቀስ​ተ​ኛው ቀስ​ቱን ይገ​ትር፤ ለጐ​በ​ዛ​ዝቷ አት​ዘኑ፤ ሠራ​ዊ​ቷ​ንም ሁሉ አጥፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በወርዋሪው ላይ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፥ ለጐበዛዝትዋ አትዘኑ ሠራዊትዋንም ሁሉ አጥፉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 51:3
12 Referencias Cruzadas  

ሕፃኖችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።


ፈረሰኞች ሆይ! ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፥ ራስ ቁርንም ደፍታችሁ በቦታችሁ ቁሙ፤ ጦርንም ሰንግሉ ጥሩርንም ልበሱ።


እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ፥ ባቢሎንን ዙሪያዋን ክበቡ፤ በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት ፍላጻንም አታስቀሩ።


በምራታይም ምድር ላይ በፋቁድም በሚኖሩት ላይ ውጣ፤ ግደላቸው ፈጽመህም አጥፋቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዳዘዝሁህም ሁሉ አድርግ።


ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ ደርሶአልና ወዮላቸው!


ምንም እንኳ ባቢሎን ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ የኃይልዋንም ከፍታ ብታጠናክር፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል ጌታ።


ሕፃናቱን ከመንገድ ጉልማሶቹንም ከአደባባይ ለማጥፋት ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ ንጉሥ ቅጥሮቻችን ውስጥ ገብቶአል።


ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ በየመንገዱ ላይ በጦርነት፥ በቤትም ውስጥ በድንጋጤ ያጠፋቸዋል።


ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታልና፤ ምሕረትም ፍርድን ያሸንፋል።