እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፦ “የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፥ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና፥ እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
ኤርምያስ 51:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፥ በመዝገቦችም የበለጠግሽ ሆይ! የእንጀራሽ ገመድ ተበጥሶዋል ፍጻሜሽ ደርሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ በብዙ ውሃ አጠገብ የምትኖሪ፣ በሀብትም የበለጸግሽ ሆይ፤ የምትወገጂበት ጊዜ ወጥቷል፤ ፍጻሜሽ ደርሷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ በታላላቅ ወንዞች አጠገብ የምትኖሪ ሀብታሚቱ ባቢሎን ሆይ! የተወሰነብሽ የመጥፊያሽ ዘመን ደርሶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፥ በመዝገብም የበለጠግሽ ሆይ! እንደ ስስትሽ መጠን ፍጻሜሽ ደርሶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፥ በመዝገብም የበለጠግሽ ሆይ፥ እንደ ስስትሽ መጠን ፍጻሜሽ ደርሶአል። |
እግዚእብሔርም ኖኅን አለው፦ “የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፥ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና፥ እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከላዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።
በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ ባለጠግነትንም በቅን ባልሆነ መንገድ የሚሰበስብ ሰው እንዲሁ ነውና፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ።
ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሙግትሽን እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም አደርቀዋለሁ ምንጭዋንም እንዲደርቅ አደርጋለሁ።
እርሱም፦ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “የበጋ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት ነው” አልኩት። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቷል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ አላልፋቸውም።
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!
ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ሴት ፍርድ አሳይሃለሁ፤
በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከሀብቷ የተነሣ ሀብታም ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።