አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።
ኤርምያስ 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በዚያ ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ፈጽሜ አላጠፋችሁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይሁን እንጂ፣ በዚያ ዘመን እንኳ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈጽሜ አላጠፋችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህም ሁሉ ሲሆን በእነዚያ ቀኖች እንኳ ሕዝቤን ጨርሼ አላጠፋም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን “በዚያ ዘመን ይላል እግዚአብሔር፤ ፈጽሜ አላጠፋችሁም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በዚያ ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈጽሜ አላጠፋችሁም። |
አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።
መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፤ የምትተማመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደመስሳሉ።
እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፦ “አምላካችን ጌታ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለምን አደረገብን?” ቢሉ፥ አንተ፦ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳገለገላችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች ታገለግላላችሁ” ትላቸዋለህ።
ትንቢት እየተናገርሁ ሳለሁ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፥ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወዮ! የእስራኤልን ትሩፍ ፈጽመህ ታጠፋለህን?
እነርሱ ሲገድሉ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ ጮኽሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ትሩፍ ሁሉ ታጠፋለህን?
ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው።