መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
ኤርምያስ 48:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንደ ተናገረው፥ አጥፊው ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፤ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም እንዳልነበረ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤ አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ሸለቆው ይጠፋል፤ ዐምባውም ይፈርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንደ ተናገረ አጥፊው በከተሞች ሁሉ ላይ ይመጣል፤ አንድም የሚያመልጥ ከተማ የለም። ሸለቆውንና ሜዳውን እንዳልነበሩ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ ጥፋት ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል፤ አንዲትም ከተማ አትድንም፤ ሸለቆውም ይጠፋል፤ ሜዳውም ይበላሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ አጥፊ ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፥ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም ይበላሻል። |
መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።
የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ! ማቅ ልበሺ፥ በአመድም ውስጥ ተንከባለዪ፤ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፥ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም ሴዎንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርን፥ ሪባን ድል ነሣቸው።