ኤርምያስ 48:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሚያገላብጡትን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እነርሱም ያገላብጡታል፤ ጋኖቹንም ባዶ ያደርጋሉ፥ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር። “እነርሱም ይደፉታል፤ ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤ ማንቈርቈሪያዎቹንም ይሰባብራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው የወይን ጠጅን ከአንድ ዕቃ ወደ ሌላ ዕቃ ገልብጦ ባዶውን ዕቃ እንደሚሰብር፥ እኔም ሞአብን የሚያወድምና ሕዝብዋን የሚያፈልስ ሰው የምልክበት ጊዜ በእርግጥ ተቃርቦአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ ጠማሞችን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ይጠሙበታል፤ ጋኖቹንም ይቀጠቅጣሉ፤ ፊቀኖቹንም ይሰብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሚያገላብጡትን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያገላብጡታል፥ ጋኖቹንም ባዶ ያደርጋሉ፥ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ። |
የሸክለኛ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፥ ሳይራራም ያደቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት፥ ወይም ውኃ ከጉድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።
ታላላቆቻቸውም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ላኩ፤ ወደ ጉድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።
“ልትታረዱና ልትበተኑ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።
እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ሞዓብ ከብላቴንነቱ ጀምሮ ተረጋግቷል፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃም ወደ ዕቃ አልተንቈረቈረም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፤ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም።