በዚያን ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፤ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፤ ከእንግዲህ ወዲህ በመታቸው ላይ አይታመኑም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ፤ በእውነት ይታመናሉ።
ኤርምያስ 44:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም በግብጽ ምድር በዚያ ለመቀመጥ ከገቡት ከይሁዳ ትሩፍ ማናቸውም ተመልሰው ለመቀመጠጥ ወደ ሚመኙበት ወደ ይሁዳ ምድር አያመልጡም በሕይወትም አይተርፉም አይመለሱምም፤ ከአንዳንድ ከሚያመልጡ በቀር አይመለሱም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ግብጽ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በይሁዳ ከስደት ተርፈው ወደ ግብጽ ወርደው ከሚኖሩት መካከል አንድ እንኳ የሚያመልጥ ወይም የሚተርፍ አይኖርም፤ እንደገና ይኖሩባት ዘንድ ወደሚናፍቋት ወደ ይሁዳ የሚመለስ ማንም አይኖርም፤ ከጥቂት ስደተኞች በቀር ተመልሶ የሚመጣ አይኖርም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ለመቀመጥ በልባቸው ተስፋ ወደሚያደርጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሱ ዘንድ በግብፅ ለመኖር ከመጡ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፥ ወደዚያም የሚመለስ አይኖርም፤ ከሚያመልጥም በቀር ማንም አይመለስም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ለመቀመጥ ወደ ግብጽ ምድር ከሄዱ፥ ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው በዚያ ይቀመጡ ዘንድ ከሚወድዱ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር ወደዚያም የሚመለስ የለም፥ ከሚያመልጥም በቀር ማንም አይመለስም። |
በዚያን ቀን ከእስራኤል ዘር የተረፉት፤ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት፤ ከእንግዲህ ወዲህ በመታቸው ላይ አይታመኑም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ፤ በእውነት ይታመናሉ።
ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታሉ፤ እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ከእነርሱ አንድም ሰው በሕይወት አይተርፍም፥ አንድም ሰው አያመልጥም።
ስለዚህ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ‘ሕያው በሆነ ጌታ እግዚአብሔር እምላለሁ!’ ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ።
ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።