ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።
ኤርምያስ 32:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጌታም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ ‘በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፤ የርስቱና የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና፤ ለአንተ ግዛው’ አለኝ። ይህም የጌታ ቃል እንደሆነ አወቅሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ፣ የአጎቴ ልጅ አናምኤል ወደ ዘብ ጠባቂዎቹ አደባባይ መጥቶ፣ ‘የመቤዠቱን ርስት የማድረጉ መብት የአንተ ስለ ሆነ፣ በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን መሬቴን ለራስህ እንዲሆን ግዛው’ አለኝ።” ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሐናምኤል ታስሬ ወዳለሁበት ወደ ዘብ ጠባቂዎች ክፍል መጥቶ “የመግዛት መብት ያንተ ስለ ሆነ መሬቴን ግዛ” አለኝ፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ ዐወቅሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ እግዚአብሔርም ቃል የአጎቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወደ አለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፥ “በብንያም ሀገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ፤ የመግዛትና የመውረስ መብቱ የአንተ ነውና፥ አንተ ታላቃችን ነህና፤ ለአንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ እግዚአብሔርም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፥ ርስቱ የአንተ ነውና፥ መቤዠቱም የአንተ ነውና፥ ለአንተ ግዛው አለኝ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ አወቅሁ። |
ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።
እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
በዚያን ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በእስር ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።
ምንም እንኳ ከተማይቱ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ ብትሰጥም፤ አቤቱ ጌታ ሆይ! አንተ ግን፦ “እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ” አልኸኝ።’ ”
እነሆ፥ የአጐትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘በመግዛት የመቤዠት መብት የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ’ ይልሃል።
እኔም እንደታዘዝኩት አደረግሁ፥ በቀንም ጓዙን እንደ ስደተኛ ጓዝ አወጣሁ፥ በምሽትም ጊዜ ግንቡን በእጄ ቦረቦርሁት፥ እያዩኝም በትከሻዬ ላይ ተሸክሜ በጨለማ አወጣሁት።