ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር “ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል።
ኤርምያስ 31:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ የተጠረሱ ይሆናሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል፤ ጐምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የራሱን ጥርስ ይጠርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ መሆኑ ቀርቶ ጎምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የገዛ ራሱን ጥርስ ብቻ ያጠርሳል፤ እያንዳንዱም በገዛ ራሱ ኃጢአት ይሞታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ ጮርቃውን የወይን ፍሬ የሚበላም ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፥ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ። |
ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር “ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል።
ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች፥ ልጅ የአባትን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጅን ኃጢአት አይሸከምም፥ የጻድቅ ሰው ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የክፉ ሰው ክፋትም በራሱ ላይ ይሆናል።
እኔ ጻድቁን፦ በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ጽድቁን ተማምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአትም ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።
ኃጢአተኛውን ሰው፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ በምለው ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ባታስጠነቅቀው ያ ኃጢአተኛ ሰው በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።