La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 25:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ደግሞ እነርሱን ይገዙአቸዋል፤ እኔም እንደ አድራጎታቸውና እንደ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቧም ለብዙ ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት ባሮች ይሆናሉ፤ እንደ አድራጎታቸውና እንደ እጃቸውም ሥራ እከፍላቸዋለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ባቢሎናውያን ስላደረጉትም ክፋት ሁሉ ቅጣታቸውን እንዲያገኙ አደርጋለሁ፤ ብዙ ሕዝቦችና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያ አድርገው ይገዙአቸዋል።’ ”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እነርሱን ያስገዙአቸዋል፥ እኔም እንደ አደራረጋቸውና እንደ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 25:14
17 Referencias Cruzadas  

አንቺ ፈራሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።


በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።


አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፥ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፥ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።


የጩኸት ድምፅ ከከተማ፥ ድምፅም ከመቅደስ፥ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የጌታ ድምፅ ተሰምቶአል።


በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።


በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ዐይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።


እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤ ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ዳርቻ ይነሣሉ።


እነሆ፥ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርሷም ላይ ይሰለፋሉ፥ ከዚያም ትያዛለች፤ ፍላጾቻቸውም ተጨናግፎ ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ጀግና ፍላጻ ናቸው።


ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፥ የጌታ የበቀል ጊዜ በእርሷ ላይ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


የበቀል ወራት መጥቷል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ይወቀው፤ ከበደልህና ከጥላቻህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሞኝ ሆኗል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።