ኤርምያስ 24:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ ጌታ አሳየኝ፥ እነሆም፥ በጌታ መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ የኢዮአቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንንና ባለሥልጣኖቹን እንዲሁም የይሁዳን የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ብረት ቀጥቃጮች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው በኋላ፣ እግዚአብሔር ሁለት ቅርጫት በለስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጦ አሳየኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ፍሬ ቅርጫቶችን አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮአቄም ልጅ የሆነውን የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳ መሪዎች፥ ከእጅ ጥበብ ባለሞያዎችና ከሌሎችም ብልኀተኞች ሠራተኞች ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን አስሮ ከወሰደ በኋላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ እግዚአብሔር አሳየኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር። |
ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
እነዚህም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን መሳፍንት ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ያልወሰዳቸው ዕቃዎች ነበሩ፤
ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና፥ የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና፥ ይላል ጌታ።”
ነቢዩ ኤርምያስ ተማርከው ወደ ተረፉት ሽማግሌዎች፥ ወደ ካህናቱም፥ ወደ ነቢያቱም፥ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃላት ይህ ነው።
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን እናቱም እቴጌይቱና ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች፥ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
በመንጠቆዎችም አድርገው በቀፎ ውስጥ አኖሩት፥ ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግመኛ እንዳይሰማ ወደ እስር ቤት አመጡት።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ መከር ካለፈ በኋላ ያለው እህል በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፤ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለ ነበረ።