ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
ኤርምያስ 2:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ኰረዳ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጣጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን በቍጥር ለማይቆጠሩ ቀናቶች ረስተውኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን፣ እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ኰረዳ ጌጣጌጥዋን፥ ሙሽራም የሙሽርነት ልብስዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ሊቈጠሩ ለማይችሉ ለብዙ ዘመናት ረስተውኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ሙሽራ ጌጥዋን ወይስ ድንግል ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠር ወራት ረስቶኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል። |
ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
ቀለበቱንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ “ያ ሰው እንዲህ አለኝ” ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፥ እነሆም፥ በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።
ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሽው፥ በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው፥ ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፥ አንቺም አልፈራሽም።
አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
ቃሌን ለመስማት እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ሊያገለግሉአቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፥ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንደማይረባ እንደዚህ መታጠቂያ ይሆናሉ።
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል ለከንቱ ነገርም ዐጥነዋል፤ ከመንገዳቸውም አሰናክለዋቸዋል ከቀድሞውም ጐዳና ርቀው ወዳልተሠራው ወደ ጠማማው መንገድ ሄደዋል።
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።