ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።
ኤርምያስ 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምን ወለድሽኝ? ዕድል ፈንታዬ ከአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ጋር መከራከርና መነታረክ ሆኗል፤ እኔ ገንዘብ ለማንም አላበደርኩም ወይም ከማንም አልተበደርኩም፤ ሆኖም ሰው ሁሉ ይረግመኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፥ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል። |
ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።
አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፦ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን በእስራኤል ላሉት ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት እንዲሆን ተሾሞአል፤