ኤርምያስ 10:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! ገሥጸኝ፤ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ቅጣኝ፤ ብቻ በመጠኑ ይሁንልኝ፤ ፈጽሞ እንዳልጠፋ፣ በቍጣህ አትምጣብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ትክክለኛ ፈራጅ እንደ መሆንህ ገሥጸን፤ ነገር ግን ፈጽመን እንዳንጠፋ በምትቈጣበት ጊዜ አይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ቅጣን፤ ነገር ግን ፈጽመህ እንዳታጠፋን በፍርድህ ይሁን እንጂ በቍጣህ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ቅጣኝ፥ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን። |
አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።
አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም እንድትሰደድ ያደረግኹባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።”
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።