ኢሳይያስ 66:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንድትጠቡ ከማጽናናትዋም ጡት እንድትጠግቡ፥ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ እንዲላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሚያጽናኑ ጡቶቿ፣ ትጠባላችሁ፤ ትረካላችሁም፤ እስክትረኩም ትጠጣላችሁ፤ በተትረፈረፈ ሀብቷም ትደሰታላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የምታደርጉት ከመጽናኛ ጡትዋ ጠብታችሁ ትጠግቡ ዘንድ፥ ከተከበረው ደረትዋ የተትረፈረፈውን ወተት ጠጥታችሁ ትደሰቱ ዘንድ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናቷም ጡት ትጠግቡ ዘንድ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናትዋም ጡት ትጠግቡ ዘንድ፥ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ። |
ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዝቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።
በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጽግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፥ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፥ ከጌታም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፥ የሰጢምንም ሸለቆ ታጠጣለች።