ኢሳይያስ 62:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ለእርሱም ዕረፍት አትስጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሩሳሌምን እስኪያጸናት፣ የምድርም ምስጋና እስኪያደርጋት ዕረፍት አትስጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌምን እስኪመሠርታትና በምድር ሁሉ ዝነኛ ከተማ እስከሚያደርጋት ድረስ ሳታቋርጡ አሳስቡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና፥ በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ ዝም አትበሉ። |
የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”