ኢሳይያስ 61:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ ጌታ የባረከው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሮቻቸው በመንግሥታት፣ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ፤ የሚያዩአቸውም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የባረካቸው ሕዝብ እንደ ሆኑ ያውቃሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘራቸው በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ያውቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፥ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል። |
ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ ስለ አሕዛብም አለቆች እልል በሉ፤ አውጁ፥ አመስግኑ፦ ጌታ ሆይ! ሕዝብህን የእስራኤልን ትሩፍ አድን በሉ።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ በረከት መሆን እንድትችሉ አድናችኋለሁ፤ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።