እናንተን ጌታን የተዋችሁትን ግን፥ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፥ ዕጣ ፋንታ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፥ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን የቀዳችሁትን፥
ኢሳይያስ 57:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፥ እነርሱም ዕጣዎችሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቁርባን አፍስሰሻል፥ የእህልንም ቁርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮች ውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሸለቆ ለስላሳ ድንጋዮች መካከል መርጣችሁ አማልክታችን ናቸው በማለት የመጠጥና የእህል ቊርባን ታቀርቡላቸዋላችሁ። በዚህ ነገር አልቈጣምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆ ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች ዕድል ፋንታሽ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፥ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፥ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፥ የእልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣም? |
እናንተን ጌታን የተዋችሁትን ግን፥ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፥ ዕጣ ፋንታ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፥ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን የቀዳችሁትን፥
በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤
የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፥ እነዚያ በሰገነቶቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፥ እንደ ቶፌት ስፍራ የረከሱ ይሆናሉ።’ ”
ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፥ እኔንም ለማስቈጣት በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ካጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል።
እኔን ለማስቆጣት፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ፥ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ፤ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቁርባን ያፈስሳሉ።
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።
እንጨቱን “ንቃ” ዝም ያለውንም ድንጋይ “ተነሣ” ለሚለው ወዮለት! ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ በውስጡም ምንም እስትንፋስ የለበትም።