ኢሳይያስ 54:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ አንጥረኛን የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣ የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ በወናፉ ፍሙን የሚያናፋውን ብረት አቅላጭ የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ እርሱም መሣሪያውን የሚሠራው ለየተሠራለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ነው፤ ያጠፋ ዘንድ አጥፊውን የፈጠርኩ እኔ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ እንደሚያናፋ፥ ለሥራውም መሣሪያ እንደሚያወጣ ብረት ሠሪ የፈጠርሁሽ አይደለም፤ እኔ ግን ለመልካም ፈጠርሁሽ እንጂ ለጥፋት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፥ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ። |
መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።
ይህን እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? እሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግኩ።
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።
እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልኩት። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሯቸው፥ የይሁዳንም አገር ለመበተን ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊቆርጡ መጥተዋል” ብሎ ተናገረ።
ኢየሱስም መልሶ “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ኀጢአቱ የባሰ ነው” አለው።
በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው።