ኢሳይያስ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብዣቸው ላይ መሰንቆና በገና፥ አታሞና እምቢልታ፥ የወይን ጠጅም ይገኛል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሥራና ውለታውን አላስተዋሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሰንቆና በገና ከበሮና እምብልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም። |
ነገር ግን እናንተ፦ “ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣም” በማለት እነሆም፥ በሐሤትና በደስታ በሬንና በጉንም ስታርዱ፥ ሥጋንም ስትበሉ፥ የወይን ጠጅንም ስትጠጡ ነበር።
በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኩል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፤ የእርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም ለሚሉ ወዮላቸው!”
እንደዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤