ኢሳይያስ 47:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፥ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተቀበልሽው ምክር ሁሉ ድካም ብቻ ሆኖ አስቀርቶሻል! እነዚያ ከወር እስከ ወር ከዋክብትን አንጋጦ በማየት የሚተነብዩ፣ ኮከብ ቈጣሪዎች እስኪ ይምጡ፤ ከሚደርስብሽም ነገር እስኪ ያድኑሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቀበልሻቸው ምክሮች ሁሉ ያደክሙሻል እንጂ ምንም አይጠቅሙሽም፤ በየወሩ መባቻ ከዋክብትን የሚመለከቱ ኮከብ ቈጣሪዎችሽ ወደፊት ይምጡ፤ በአንቺ ላይ ከሚደርሰውም ችግር ያድኑሽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክፉ ምክርሽ ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ ይነሡ፤ ያድኑሽም፤ ምን እንደሚመጣብሽም ይንገሩሽ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፥ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፥ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ። |
የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፥ የሚያድንሽ አይገኝም።
አሁን ግን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በአንድ ቀን በድንገት ይመጡብሻል፤ ምንም መተት ብታበዥና ምንም ዓይነት አስማት ቢኖርሽም ፈጽሞ አይቀሩልሽም።
ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰፋፊዎቹ የባቢሎን ቅጥሮች ፈጽመው ይፈርሳሉ ረጃጅሞችም በሮችዋ በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሕዝቡም በከንቱ ጉልበቱን ይፈስሳል፥ አሕዛብም የደከሙበት ነገር ለእሳት ይሆናል።”
አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው።