ኢሳይያስ 47:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደሆነ፥ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በይ እንግዲህ፣ ከልጅነትሽ ጀምሮ የደከምሽባቸውን፣ አስማቶችሽን፣ ብዙ መተቶችን ቀጥዪባቸው፤ ምናልባት ይሳካልሽ፣ ምናልባትም ጠላቶችሽን ታሸብሪባቸው ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስኪ ከሆነልሽ ከሕፃንነትሽ ጊዜ ጀምሮ ስትጠቀሚባቸው የኖርሽውን ያፍዝ አደንግዝ ድግምትና የጥንቈላ መተቶችን አስቀምጪ፤ ምንአልባት ጥቂት ይረዳሽ ይሆናል፤ ወይም ጠላቶችሽን ልታስፈራሪባቸው ትችያለሽ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናልባትም ሊያድንሽ የሚችል እንደ አለ፥ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከተማርሽው ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደ ሆነ፥ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ። |
የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን፥ የሙታን መናፍስትን፥ መናፍስት ጠሪዎቻቸውንና የጠንቋዮቻቸውን ምክር ይጠይቃሉ።
ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጠምጠሚያውን አውልቅ፥ ዘውዱንም አርቅ፤ ይህ እንዲህ አይሆንም፤ የተዋረደውን ከፍ አድርግ፥ ከፍ ያለውንም አዋርድ።
ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፤ እርሷም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።