ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ኢሳይያስ 44:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም አገልጋዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህ እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አድምጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማ። |
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ አንተም አገልጋዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ያልተረሳህ ትሆናለህ።
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
“አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል ጌታ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረኩበት አገር አድናለሁና፤ ያዕቆብም ይመለሳል ያርፋልም በደኅንነትም ይቀመጣል፤ እርሱንም ማንም አያስፈራራውም።
አንበሳ ከችፍግ ዱሩ ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚያጠፋ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።
ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።